1.7 KiB
1.7 KiB
እናንተ ሰዎች እስክትደቅቁ ትሰባበራላችሁ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰራዊታችሁን እስኪደቅ እሰባብራለሁ››
በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ
ኢሳይያስ በሌላ አገር ያሉ ሰዎች እንደሚሰሙት አድርጐ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሩቅ ቦታዎች ያላችሁ ሰዎች ሁሉ አድምጡ››
ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እስክትደቅቁ ተሰባበሩ፤ ተዘጋጁ እስክትደቅቁ ተሰባበሩ
ይህ በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆንም፣ የተደጋገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሳችሁን ለጦርነት ማዘጋጀት ትችላላችሁ፤ እኔ ግን አሸንፋችኃለሁ፡፡››
ዕቅዱ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ ተመካከሩ ግን አይሳካም
ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይሁዳን ለማጥቃት መዘጋጀት ትችላላችሁ፤ ግን አይሳካላችሁም››
አይጸናም… አይሳካም
ዕቅዱን ወይም ትእዛዝን መፈጸም ዕቅዱን ወይም ትእዛዙን ያወጣው ሰው መስማት የሚፈልገውን ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማድረግ ያቀዳችሁትን ማድረግ አትችሉም… ወታደሮቻችሁም አዛዦቻቸው ያዘዟቸውን ማድረግ አይችሉም››