1.3 KiB
1.3 KiB
አጠቃላይ መረጃ
ኢሳይያስ ስለ ራእዩ መናገሩን ቀጥሏል፡፡
ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ
‹‹ሱራፌል ሲጮኹ ድምፃቸው መድረኩንና መሠረቱን አናወጠው››
ቤቱ በጢስ ተሞላ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቤተ መቅደሱን ጢስ ሞላው›› ወይም፣ ‹‹ቤተ መንግሥቱን ጢስ ሞላው››
ጠፍቻለሁ ወዮልኝ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታላቅ ችግር ውስጥ ነኝ! አስቸጋሪ ነገር ይደርስብኛል››
ከንፈሮቼ የረከሱብኝ
እዚህ ላይ፣ ‹‹ከንፈሮች›› ሰው የሚናገረውን ያመለክታሉ፡፡ ሰዎች እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ነገር መናገራቸው የከንፈሮቻቸው መርከስ ማለት እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡
ያህዌ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ
‹‹የመላእክት ሰራዊት ገዢ ያህዌ››
ዐይኖቼ ዐይተዋል
‹‹ዐይኖች›› መላውን ሰው ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አይቻለሁ››