3.0 KiB
አጠቃላይ መረጃ
ኢሳይያስ ስለ ወይኑ ቦታ ገለጻ ይሰጣል
የሰራዊት ጌታ የያህዌ የወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፡፡
ምሳሌው ውስጥ ያለው ወይን ቦታ የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚወክል ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰራዊት ጌታ የያህዌ ወይን ቦታ የእስራኤልን ቤት ይወክላል›› ወይም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ወይን ቦታ ናቸው››
የእስራኤል ቤት
‹‹ቤት›› — ቤቱ ውስጥ የሚኖረውን ቤተ ሰብ ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስራኤል›› ወይም፣ ‹‹የእስራኤል መንግሥት›› ወይም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ››
የይሁዳ ሰዎች የደስታው አትክልት ናቸው
የይሁዳ ሰዎች ያህዌ የተከለው ወይን ዛፍ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ይህን በምስስል ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ሰዎች ለያህዌ ደስታ ያህዌ እንደ ተከለው ወይን ዛፍ ናቸው››
የይሁዳ ሰዎች
‹‹ሰዎች›› የሚወክለው የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ሕዝብ››
ፍትሕን ፈለገ፤ ግን ግድያ ነበረ
እዚህ ላይ፣ ‹‹ፍትሕ›› የሚለውን፣ ‹‹መልካሙን ማድረግ›› ብሎ መለወጥ ይችላል፡፡ ‹‹ግድያ›› የሚለውን፣ ‹‹እርስ በርስ መገዳደል›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሕዝቡ መልካም ነገር እንዲያደርግ ፈለገ፤ ግን እርስ በርስ ተገዳደሉ››
ጽድቅን ፈለገ
‹‹ፈለገ›› የሚለውን በዚህ ቁጥር ከተመለከትነው መረዳት ይቻላል፡፡ ትርጒሙን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ መደጋገም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጽድቅን ፈለገ›› ወይም፣ ‹‹መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ፈለገ››
ይልቁን የጭንቅ ጩኸት ነበረ
‹‹ነበረ›› የሚለውን ቀደም ሲል ከነበረው ቁጥር መረዳት ይቻላል፡፡ ትርጒሙን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ መደጋገም ይቻላል፡፡ ሰዎች ርዳታ ለመፈለግ የጮኹበትን ምክንያት የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይልቁን የርዳታ ጩኸት ነበረ›› ወይም፣ ‹‹ይልቁን ሌሎች ስላጠቋቸው የሚረዳቸው ሰው ፍለጋ ጩኸት ነበረ››
ጩኸት
ምናልባት ብዙ ጩኸቶችን የሚያመለክት ገለጻ ሊሆን ይችላል፡፡