am_tn/isa/05/05.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ባቀረበው ምሳሌ የወይኑ ቦታ ባለቤት ስለ ወይን ቦታው መናገር ቀጥሏል፡፡

ሐረጉን እነቅላለሁ

‹‹የቁጥቋጠውን ሐረግ እነቅላለሁ›› ሐረግ መደዳውን ያለ ቁጥቋጦ ወይም የአትክልት ቦታን ወይም ሌላ ክልልን ለመጠበቅ መደዳውን የሚተከል ዛፍ ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ሐረግ›› ምናልባት ወይን ቦታው ዙሪያ ባለው ግንብ ላይ የሚተከል እሾኻማ ቁጥቋጦ ሊሆን ይችላል፡፡

የግጦሽ ቦታ እንዲሆን አደርጋለሁ

‹‹ከብቶች ገብተው የሚመገቡበት ቦታ አደርገዋለሁ›› ይህ ከብቶች የሚመገቡት ሣር የበዛበት ቦታ ነው፡፡

መረጋገጫም ይሆናል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከብቶች ይረጋግጡታል››

ጠፍ መሬት አደርገዋለሁ

‹‹አጠፋዋለሁ››

ከእንግዲህ አይኮተኮትም አይታረምም

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም አይኮተኩተውም፤ አያርመውም›› ወይም፣ ‹‹ማንም የማያስፈልጉትን ቅርንጫፎች አይቆርጥም፤ ለአፈሩም ጥንቃቄ አያደርግም››

ኩርንችትና እሾኽም ይበቅልበታል

ብዙውን ጊዜ ኩርንችትና እሾኽ ጠፍ የሆኑ ከተሞችንና አገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡