am_tn/isa/43/10.md

24 lines
1.7 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# እናንተ… የእኔ አገልጋይ
‹‹እናንተ›› ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹የእኔ አገልጋይ›› ጠቅላላ መንግሥቱን ያመለክታል፡፡
# ከእኔ በፊት… ከእኔ በኃላ
በዚህ መልኩ መናገሩ ከእርሱ በፊት የነበረና ከእርሱ በኃላም እንደሚኖር ያህዌ እየተናገረ አይደለም፡፡ እርሱ ዘላለማዊ ሲሆን፣ ሕዝቡ የሚያመልኳቸው አማልክት ግን አለመሆናቸውን እያረጋገጠ ነው፡፡
# ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም
እዚህ ላይ፣ ‹‹አልተሠራም›› ሲል ያህዌ ሕዝቡ ስለሠሩዋቸው ጣዖቶች እየተናገረ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሕዛብ ካሠሩዋቸው ጣዖቶች አንዱ እንኳ ከእኔ በፊት አልተሠሩም››
# ከእኔም በኃላ አይኖርም
‹‹ከእነዚህ አማልክት አንዱም ከእኔ በኃላ አይኖርም››
# እኔ፣ እኔ ያህዌ ነኝ
‹‹እኔ›› የሚለው ቃል የተደገመው አጽንዖቱ ያህዌ ላይ እንዲያተኩር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ብቻ ያህዌ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ራሴ ያህዌ ነኝ››
# ከእኔ ሌላ አዳኝ የለም
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አዳኝ እኔ ብቻ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እናንተን ማዳን የምችል እኔ ብቻ ነኝ››