# እናንተ… የእኔ አገልጋይ ‹‹እናንተ›› ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹የእኔ አገልጋይ›› ጠቅላላ መንግሥቱን ያመለክታል፡፡ # ከእኔ በፊት… ከእኔ በኃላ በዚህ መልኩ መናገሩ ከእርሱ በፊት የነበረና ከእርሱ በኃላም እንደሚኖር ያህዌ እየተናገረ አይደለም፡፡ እርሱ ዘላለማዊ ሲሆን፣ ሕዝቡ የሚያመልኳቸው አማልክት ግን አለመሆናቸውን እያረጋገጠ ነው፡፡ # ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም እዚህ ላይ፣ ‹‹አልተሠራም›› ሲል ያህዌ ሕዝቡ ስለሠሩዋቸው ጣዖቶች እየተናገረ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሕዛብ ካሠሩዋቸው ጣዖቶች አንዱ እንኳ ከእኔ በፊት አልተሠሩም›› # ከእኔም በኃላ አይኖርም ‹‹ከእነዚህ አማልክት አንዱም ከእኔ በኃላ አይኖርም›› # እኔ፣ እኔ ያህዌ ነኝ ‹‹እኔ›› የሚለው ቃል የተደገመው አጽንዖቱ ያህዌ ላይ እንዲያተኩር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ብቻ ያህዌ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ራሴ ያህዌ ነኝ›› # ከእኔ ሌላ አዳኝ የለም ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አዳኝ እኔ ብቻ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እናንተን ማዳን የምችል እኔ ብቻ ነኝ››