1 line
832 B
Plaintext
1 line
832 B
Plaintext
\v 7 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በመባለው በአሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን ያይህዌ ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ መጣ። \v 8 እነሆም በሌሊት ራእይ አየሁ፤ አንድ ሰው ቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በሸለቆው ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡናማና ነጭ ፈረሶች ቆመው ነበር። \v 9 እኔም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ፣ ምን እንደ ሆኑ፣ አሳይሃለሁ” አለኝ። |