\v 7 ስለዚህ እኔ ለእርድ ለተለዩትና ለተጨቆኑት እረኛ ሆንሁ። ሁለት በትሮች ወስጄ እንዱን፣ “ሞገስ” ሌላውንም፣ “አንድነት” ብዬ ጠራኋቸው። መንጋውንም አሰማራሁ። \v 8 በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ፤ ትዕግሥቴ አለቀ፤ እነርሱም እንዲሁ እኔን ጠሉኝ። \v 9 ከዚያም ለበጎቹ ባለቤቶች፣ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱ በጎች ይሙቱ፤ የሚጠፉት በጎች ይጥፉ። የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።