am_rev_text_udb/02/14.txt

1 line
777 B
Plaintext

\v 14 ያም ሆኖ ግን፣ ምስክርነትህን የሚያበላሹና ታዛዥነትህን የሚያዳክሙ አንዳንድ ነገሮች እያየሁ ነው። አንዳንድ አባሎችህ ከረጅም ጊዜ በፊት በለዓም ያስተማረውን ዓይነት ትምህርት ሲያስተምሩ ዝም እያልሃቸው ነው። እርሱ ለጣዖታት የተሠዋውን እንዲበላና በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ዝሙት እንደሚፈቅድ ባላቅን አስተማረ። \v 15 በዚያ መንገድ አንተም አንዳንድ አባሎችህ የኒቆላውያንን ትምህርት እንዲለማመዱና ያልተፈቀደው ዝሙት እንደ ተፈቀደ ሲያስተምሩ ዝም እያልሃቸው ነው።