am_rev_text_udb/02/08.txt

1 line
1.2 KiB
Plaintext

\v 8 “በሰምርኔስ ከተማ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ ይህን መልእክት ጻፍ፤ ‘እነዚህ ነገሮችን ለእናንተ እናገራለሁ፤ እኔ ነገሮችን ሁሉ የጀመርሁ የመጀመሪያ ነኝ፤ ነገሮች ሁሉ እንዲያበቁ የማደርግ የመጨረሻውም ነኝ። እኔ ሞቼ የነበርሁትና እንደ ገና በሕይወት ያለሁት ነኝ። \v 9 ምን ያህል መከራ እንደ ተቀበልህ አውቃለሁ። ድኽነትህንና ብዙ ነገሮች የጎደሉህ መሆኑን አውቃለሁ (ሆኖም፣ ዘላለማዊና በፍጹም ከአንተ የማይወሰዱ ነግሮችን በተመለከተ በእርግጥ ሀብታም ነህ)። ክርስቶስን በመከተልህ በሰዎች መሰደብና ስለ አንተ ብዙ መጥፎ ነገሮች መወራታቸው ምን ማለት እንደ ሆነ ታውቃለህ። እነዚያ አንተን የሚሳደቡና ስለ አንተ መጥፎ ወሬ የሚያወሩ፣ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሰይጣን ማኅበር አባሎች እንጂ፣ የቤተ ክርስቲያን ወገን አይደለም።