am_rev_text_udb/14/17.txt

1 line
551 B
Plaintext

\v 17 ሌላም መልአክ በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። \v 18 ከመሠዊያው አንድ ሌላ መልአክ ወጣ። መሠዊያው ላይ ላለው እሳት ኀላፊነቱ የእርሱ ነበር። ማጭድ ለያዘው መልአክ በታላቅ ድምፅ፣ “ዘለላው ስለ በሰለ ማጭድህን ያዝና በምድር ያለውን የወይን ዘለላ እጨድ! ፍሬዎቹ ስለ በሰሉ ዘለላዎቹን ሰብስብ!” በማለት ጮኸ።