am_rev_text_udb/01/04.txt

1 line
1.3 KiB
Plaintext

\v 4 እኔ ዮሐንስ ይህን መልእክት በእስያ አውራጃ ላሉ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት እጽፋለሁ። እግዚአብሔር ቸር ይሁንላችሁ፤ ሰላሙንም ይስጣችሁ፣ ምክንያቱም እርሱ ሁሌም የነበረ፣ አሁን ያለና ወደ ፊትም ለዘላለም የሚኖር ነው። በዙፋኑ ፊት የሚቀመጡ ሰባቱ መናፍስት እንዲሁ ያድርጉላችሁ። \v 5 እግዚአብሔርን በተመለከተ በታማኝነት እውነቱን የነገረን ኢየሱስ ክርስቶስም ቸር ይሁንላችሁ፤ ሰላምንም ይስጣችሁ። እርሱ እግዚአብሔር በመጀምሪያ ከሙታን ያስነሣው ነው፤ በምድር ነገሥታትም ላይ የሚፈርድ እርሱ ነው። መስቀል ላይ በሞተ ጊዜ የወደደንና ኃጢአት ካስከተለው በደለኝነት በደሙ ነጻ ያወጣን እርሱ ነው። \v 6 በመንግሥቱ የሚገዛ እርሱ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡና እርሱ እንዳዘዘው ለአባቱ የሚሰግዱካህናት እንድንሆን የለየን እርሱ ነው። ለዘላለም ማክበርና ማመስገን የሚገባን ኢየሱስ ክርስቶን ነው። እውነቱ ይኸው ነው።