am_rev_text_udb/17/16.txt

1 line
696 B
Plaintext

\v 16 ያየሃቸው አሥር ቀንዶች ገዦችን ይወክላሉ። እነርሱና አውሬው ሴትዮዋን ይጠሉዋታል። እርቃን የማስቀረት ያህል በከተማው ያለ ማንኛውንም ነገር ይወስዳሉ። ሥጋዋን የመብላት ያህል ጨርሶ ያጠፏታል፤ እስክትወድም ድረስ በእሳት ያቃጥሏታል። \v 17 ያንን የሚያደርጉት እግዚአብሔር የሚፈልገውን ያደርጉ ዘንድ ስላነሣሣቸው ነው። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር የተናገረው እስኪፈጸም ድረስ የገዢነት ሥልጣናቸውን ለአውሬው ይሰጣሉ።