am_rev_text_udb/17/03.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 3 ቀጥሎም መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወሰደኝ። እዚያም ቀዩ አውሬ ላይ ተቀምጣ የነበረችውን ሴት አየሁ። በአውሬው መላ አካላት ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድቡ ስሞች ተጽፈው ነበር። አውሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት። \v 4 ሴትዮዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ ነበር፤ በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች አጊጣ ነበር፤ በእጇም የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር። ጽዋው ዝሙት በምታደርግበት ጊዜ የሚጠጣውን በሚወክል ጸያፍ ነገርና ርኵሰት ተሞልቶ ነበር። \v 5 ግንባሯም ላይ ምሥጢራዊ ትርጕም ያለው ስም ተጽፎ ነበር። ጽሑፉ፣ “ይህች እጅግ ዐመፀኛዋ ከተማ ባቢሎን ናት! የምድር አመንዝራዎች ሁሉ እናት ናት። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ርኵስና ጸያፍ ነገር እንዲያደርጉ የምድር ሰዎችን የምታስተምር እርሷናት” የሚል ነበር።