am_rev_text_udb/16/17.txt

1 line
1.0 KiB
Plaintext

\v 17 ከዚያም ሰባተኛው መልአክ ጽዋው ውስጥ የነበረውን ወይን ጠጅ አየሩ ላይ አፈሰሰ። ከዚህም የተነሣ ከቤተ መቅደሱ አንድ ታላቅ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር ዐመፀኞችን የሚቀጣበት ጊዜ ተፈጸመ” አለ። \v 18 መልአኩ ጽዋው ውስጥ የነበረውን እንዳፈሰሰ መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጎድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ሰዎች በዚህ ምድር መኖር ከጀመሩ አንሥቶ እንዲህ ያለ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም። \v 19 ከዚህም የተነሣ ታላቂቱ ከተማ ለሦስት ተከፈለች። የሌሎች መንግሥታትንም ከተሞች እግዚአብሔር አወደመ። የባቢሎን ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ማድረጋቸውን እግዚአብሔር አልዘነጋም። ስለሆነም በጣም በመቆጣት መከራ የሚያመጣባቸውን የጽዋውን ወይን ጠጅ እንዲጠጡ አደረገ።