am_rev_text_udb/16/04.txt

1 line
1.0 KiB
Plaintext

\v 4 ሦስተኛው መልአክ ጽዋው ውስጥ የነበረውን ወይን ጠጅ ወንዞችና የውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ። ከዚህም የተነሣ የወንዞችና የምንጮች ውሃ ወደ ደም ተለወጠ። \v 5 ከዚያም ውሆች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የነበርህና ያለህ ቅዱሱ ነህ። ሰዎች ላይ በጽድቅ ትፈርዳለህ። \v 6 አንተ ላይ ያመፁ ሰዎች ቅዱሳንህንና ነቢያቶችህን ገደሉ። ስለዚህ ደም እንዲጠጡ በማድረግ ስለ ቀጣሃቸው አንተ ትክክል ነህ፤ ለእነርሱ የሚገባውም ይኸው ነው” አለ። \v 7 ከዚያም አንድ ድምፅ ከመሠዊያው፣ “አዎን፣ ሁሉን ቻይ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በትክክልና በጽድቅ ሰዎች ላይ ትፈርዳለህ” የሚል ምላሽ ሰጠ።