am_rev_text_udb/16/02.txt

1 line
383 B
Plaintext

\v 2 የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ ጽዋው ውስጥ የነበረውን ወይን ጠጅ ምድር ላይ አፈሰሰ። ከዚህም የተነሣ የአውሬው አገልጋዮች የአውሬውን ስም በላያቸው እንዲጽፉ በፈቀዱት፣ ለአውሬውም ምስል በሰገዱት ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቁስል ወጣባቸው።