am_rev_text_udb/06/09.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 9 በጉ አምስተኛውን ማኅተም ሲፈታ የእግዚአብሔርን መልእክት በማመናቸውና ስለ ኢየሱስ እውነቱን ለሌሎች በመናገራቸው የተገደሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ነፍሶች በሰማይ ከመሠዊያው በታች አየሁ። \v 10 “ሉዓላዊ ጌታ፣ አንተ ቅዱስና እውነተኛ ነህ። እኛን የገደሉ በምድር ያሉ ሰዎችን የማትፈርድባቸውና የማትቀጣቸው እስከ መቼ ነው?” በማለት በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔር ይጠይቁ ነበር። \v 11 ከዚያም እግዚአብሔር ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ሰጣቸው፤ እንዲያርፉና ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሡ ነገራቸው። ከእነርሱ ጋር ጌታን ያገለገሉ አማኞችን ሁሉ ክፉ ሰዎች እስኪገድሏቸው ድረስ መታገሥ ነበረባቸው። እነርሱ በሞቱበት መንገድ እነዚህ አማኞችም እንዲሞቱ እግዚአብሔር ይፈልጋል።