am_rev_text_udb/04/07.txt

2 lines
767 B
Plaintext
Raw Normal View History

\v 7 \v 8 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ይመስል ነበር። ሁለተኛው ሕያው ፍጡር በሬ ይመስል ነበር። ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው። አራተኛው ሕያው ፍጡር እየበረረ ያለ ንስር ይመስል ነበር። አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ አራት ክንፎች ነበሯቸው። ክንፎቻቸው ከላይና ከታች በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። ቀንም ሆነ ሌሊት ያለ ማቋረጥ እንዲህ ይላሉ፤
“ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ እርሱ ሁሌም የነበረ፣ አሁንም ያለና ለዘላለም የሚኖር ነው”።