am_rev_text_udb/13/15.txt

2 lines
873 B
Plaintext
Raw Normal View History

\v 15 ደግሞም የመጀመሪያው አውሬ ምስል መናገር እንዲችል ለምስሉ እስትንፋስ ለመስጠትና ለዚህ ምስል የማይሰግዱ ሁሉ እንዲገደሉ ለማድረግ እግዚአብሔር ለሁለተኛው አውሬ ፈቀደ።
\v 16 እንዲሁም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድኾች፣ ጌቶችና ባሮች ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ የመጀምሪያውን አውሬ ስም እንዲጻፍ ሁለተኛው አውሬ ሰዎችን አስገደደ። \v 17 ሁለተኛው አውሬ እንዲህ ያደረገው ምልክቱ ማለትም የአውሬው ስም ወይም ስሙን የሚወክለውን ቊጥር ያልተቀበሉ ሰዎች ምንም ነገር መግዛትና ምንም ነገር መሸጥ እንዳይችሉ ነው።