am_num_text_ulb/22/18.txt

1 line
853 B
Plaintext
Raw Permalink Normal View History

\v 18 በለዓለም ለባላቅ ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “ባላቅ ብርና ወርቅ የሞላበትን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን ከአምላኬ፣ ከያህዌ ቃል አልፌ መሄድ አልችልም፣ ደግሞም እርሱ ከነገረኝ አሳንሼ ወይም ጨምሬ አላደርግም፡፡ \v 19 ስለዚህ አሁን፣ እባካችሁ ያህዌ የሚለኝን ተጨማሪ ነገር አውቅ ዘንድ ዛሬ ምሽትም ደግሞ በዚህ እደሩ፡፡” \v 20 እግዚአብሔር በምሽት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ እስከ መጡ ድረስ ተነስተህ ከእነርሱ ጋር ሂድ፡፡ ነገር ግን እንድታደርገው የምነግርህን ብቻ አድርግ፡፡”