am_neh_text_ulb/05/18.txt

1 line
644 B
Plaintext

\v 18 በየቀኑ አገልጋዮቼ አንድ በሬ፣ ስድስት ሙክቶች እና የዶሮዎች ስጋ እንዲያቀርቡ አደርግ ነበር፡፡ በየአስሩ ቀን ብዙ የሆነ አዲስ ወይን ጠጅ አቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ እጅግ ብዙ ግብር በመክፈል ጫና እንደሚበዛበት አውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንደ አገረ ገዥ የተፈቀደልኝን ገንዘብ እንኳን አልቀበልም ነበር፡፡ \v 19 አምላኬ፣ አስበኝ፣ እናም ለዚህ ህዝብ ላደረግኩት ሽልማት ስጠኝ፡፡