am_mrk_text_ulb/13/07.txt

1 line
481 B
Plaintext

\v 7 ጦርነትንና የጦርነትን ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትታወኩ፤ እነዚህ ነገሮች የግድ መፈጸም አለባቸው፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ \v 8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የምድር መንቀጥቀጥ፣ ረሃብም ይሆናል፡፡ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡