am_mrk_text_ulb/12/28.txt

1 line
805 B
Plaintext

\v 28 ከጸሓፍት አንዱ መጣና በአንድነት ሆነው ሲጠይቁት እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደ መላሰላቸው አይቶ፣ ከሕግ ፊተኛው የትኛው ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው፡፡ \v 29 ኢየሱስም ፊተኛው፣ እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ \v 30 አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፣በፍጹም አሳብህ፣ በፍጹምም ኀይልህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ \v 31 ሁለተኛዋም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ ከእነዚህ የሚበልጥ ምንም ሌላ ትእዛዝ የለም አለው፡፡