am_mrk_text_ulb/09/20.txt

1 line
530 B
Plaintext

\v 20 ወደ እርሱም አመጡለት፤ ባየውም ጊዜ ወዲያው መንፈሱ በምድር ላይ በኃይል ጥሎ እያንፈራገጠ አረፋ አስደፈቀው፡፡ \v 21 ኢየሱስም የልጁን አባት ይህ ከያዘው ምን ያህል ጊዜ ሆነው? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም ከሕጻንነቱ ጀምሮ ነው፡፡ \v 22 ብዙ ጊዜ ሊያጠፋው በውሃና በእሳት ላይ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ እዘንልንና እርዳን አለው፡፡