am_mrk_text_ulb/05/18.txt

1 line
659 B
Plaintext

\v 18 ጀልባዋ ውስጥ እየገባ ሳለ፣ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከአንተ ጋር ልኑር ብሎ ለመነው፡፡ \v 19 አልፈቀደለትም፤ ይልቁንም ወደ ቤትህ፣ ወደ ዘመዶችህ ሂድ፣ ጌታ ለአንተ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገልህ፣ እንዴትም ምሕረቱን ባንተ ላይ እንዳሳየ ንገራቸው አለው፡፡ \v 20 ሄደና ኢየሱስ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገለት ዐሥር ከተማ በሚባለው ውስጥ ማሠራጨት ጀመረ፤ ሰዎችም ሁሉ ተደነቁ፡፡