\v 40 ማንም ሰው ሊከስስህና ኮትህን ሊወስድ ቢመኝ፣ ካባህንም ይውሰድ። \v 41 አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ማንም ሰው ቢያስገድድህ፣ ዐብረኸው ሁለት ምዕራፍ ሂድ። \v 42 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ ከአንተ መበደር ከሚፈልገውም ፊትህን አታዙር።