\v 17 ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ልሽራቸው ሳይሆን ልፈጽማቸው ነው። \v 18 ምክንያቱም፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ፣ ሁሉ እስኪፈጸምም ድረስ፣ ከሕግ እንዷ ፊደል ወይም ቅንጣት ከቶ አታልፍም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።