\v 22 ከዚያም በአጋንንት የተያዘን ዐይነ ስውርና ዲዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም ፈወሰው፤ ዲዳውም ተናገረ፣ አየም።
\v 23 ሕዝቡም በመገረም፣ ''ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?'' አሉ፡፡