10. ሰው ልኮ ፣በወህኒ ቤትም የዮሐንስን ራስ አስቆረጠ።
11. ከዚያም ራሱ በሰሃን ተደርጎ መጥቶ ለልጁቷ ተሰጣት ፤እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።
12. ከዚያም የርሱ ደቀመዛሙርት መጥተው ፣በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህም በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።