am_mat_text_ulb/26/73.txt

1 line
632 B
Plaintext

\v 73 ጥቂት ቆየት ብሎ እዚያ ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን፣ ‹‹በእርግጥ አንተም ብትሆን ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ አነጋገርህ ራሱ ያጋልጥሃል›› አሉት፡፡ \v 74 ያኔ፣ ‹‹ሰውየውን ጨርሶ አላውቀውም›› በማለት ይራገምና ይምል ጀመር፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፡፡ \v 75 ጴጥሮስ ‹‹ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ ትክደኛለህ›› በማለት ኢየሱስ የተናገረውን አስታወሰ፡፡ ከዚያ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡