\v 71 ከግቢው ወደሚያስወጣው በር እየሄደ እያለ፣ ሌላ አገልጋይ ልጅ አየችውና እዚያ ለነበሩት፣ ‹‹ይህኛውም ሰውየ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ›› አለች፡፡ \v 72 እርሱም፣ ‹‹ሰውየውን አላውቀወም›› በማለት በመሐላ ጭምር በድጋሚ ካደ፡፡