am_mat_text_ulb/13/54.txt

3 lines
632 B
Plaintext

54. ከዚያም ኢየሱስ ወደ ራሱ አገር መጥቶ ፣ለህዝቡ በምኩራቦች አስተማረ፣ ከዚህም የተነሳ ተገርመው፥ ይህ ሰው ይህን ጥበቡንና እነዚህን ተአምራት ከየት አገኘ? አሉ።
55. ይሄ የአናጢው ልጅ አይደለም ወይ? እናቱስ ማሪያም አይደለችም ወይ? ያዕቆብ፥ ዮሴፍ ፥ስምኦን እና ይሁዳስ ወንድሞቹ አይደሉም ወይ?
56. እህቶቹስ ከእኛው ጋር አይደሉም ወይ? ታዲያ ይሄ ሰው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከየት አገኛቸው?''