am_mat_text_ulb/15/29.txt

1 line
767 B
Plaintext

\v 29 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡ \v 30 ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡ \v 31 ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ ዐይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡