am_mat_text_ulb/19/10.txt

1 line
713 B
Plaintext

\v 10 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ ‹‹የባልና የሚስት ጕዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም›› አሉት፡፡ \v 11 ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡ \v 12 በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡››