\v 34 ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰባሰቡ፡፡ \v 35 ሕግ ዐዋቂ የሆነ ከእነርሱ መካከል አንዱ እርሱን ለመፈተን፣ \v 36 ‹‹መምህር፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው›› ብሎ ጠየቀው፡፡