\v 20 ኢየሱስም፣ ‹‹ይኼ የማን መልክና ስም ነው?›› አላቸው፡፡ \v 21 እነርሱም፣ ‹‹የቄሳር፣›› አሉት፡፡ ኢየሱስም፣ ‹‹እንግዲያስ የቄሳር የሆነውን ለቄሳር ስጡ፤ የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር ስጡ›› አላቸው፡፡ \v 22 ያንን ሲሰሙ ተገረሙ፡፡ ትተውትም ሄዱ፡፡