21. ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ፣ለሞትአሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ተነሥተው ያስገድሏቸዋል። 22. ከስሜ የተነሣ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ነገር ግን ማንም እስከመጨረሻ የሚጸና እሱ ይድናል። 23. በዚች ከተማ ውስጥ ሲያሳድዷችሁ ወደሚቀጥለው ከተማ ሽሹ።እውነቱን ልንገራችሁ! የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት ፣የእስራኤልን ከተሞች አታዳርሱም።