\v 37 ጻድቃንም እንዲህ ይመልሱለታል፣ ‘ጌታው፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው? \v 38 38 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቁተህ ያለበስንህ መቼ ነው? \v 39 ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?’ \v 40 ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል ‘እውነት ነው የምላችሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’