\v 22 አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤ \v 23 ናዝሬት በምትባል ከተማ ውስጥም ኖረ፡፡ ይህ በነቢዩ ተነግሮ የነበረውን፣ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለውን እንዲፈጸም አደረገ፡፡