\v 10 \v 7 ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። \v 8 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል። \v 9 ከእናንተ መካከል ልጁ እንጀራ ሲለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጠው፣\v 10ወይስ ዐሣ ሲለምነው፣ እባብ የሚሰጠው? ምን ዐይነት ሰው ነው?