\v 22 ኢየሱስ ግን መልሶ፣ "የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?" አለ። እነርሱ፣ "እንችላለን" አሉት። \v 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በርግጥ ጽዋዬን ትጠጣላችሁ። በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ ግን እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ለእነርሱ ነው።" \v 24 ሌሎቹ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በሁለቱ ወንድማማች ላይ ተቈጡ።