\v 5 ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ \v 6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡ \v 7 ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡