27. ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፥ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት ፥ያለ ማቋረጥም ''የዳዊት ልጅ ምሕረት አድርግልን!'' እያሉ ይጮኹ ነበር። 28. ኢየሱስም ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ፥ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ ኢየሱስም ''ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?'' አላቸው። እነሱም ''አዎ! ጌታ አሉት፡፡''