\v 35 ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ። \v 36 ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው።