am_luk_text_ulb/10/40.txt

1 line
750 B
Plaintext

\v 40 ማርታ ግን ምግብ ለማዘጋጀት ባደረገችው ጥረት በጣም ውጥረት በዛባት፡፡ ወደ ኢየሱስም ዘንድ መጥታ፡- ‹‹ጌታ ሆይ፣ እኔ ብቻዬን ሥራ ስሠራ፣ እህቴ እኔን ሳትረዳኝና ስትተወኝ አንተ ዝም ትላለህን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት›› አለችው፡፡ \v 41 ጌታ ግን፡- ‹‹ማርታ፣ ማርታ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፣ \v 42 የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው፡፡ ማርያም በጣም ትክክል የሆነውን ምርጫ መርጣለች፣ ይህም ደግሞ ከእርሷ አይወሰድባትም›› ብሎ መለሰላት፡፡