am_luk_text_ulb/07/21.txt

1 line
810 B
Plaintext

\v 21 \v 22 \v 23 21-23 በዚያኑ ሰዓት ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከተለያየ ደዌና በሽታ ፈወሰ። በአጋንንት የተያዙትን ነጻ አወጣ፣ ዐይነ ስውራንም ማየት እንዲችሉ አደረገ። ኢየሱስ መልእክተኞቹን፣ “ወደ ዮሐንስ ተመልሳችሁ ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ዐይነ ስውራን ያያሉ፣ ሽባዎች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም ወንጌል እየተሰበከ ነው። በማደርጋቸው ነገሮች በእኔ ሳይሰናከል በእምነቱ የሚጸና ሰው የተመሰገነ ነው” አላቸው።