\v 8 ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡና እነርሱም ሲቀበሏችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ፡፡ \v 9 በዚያም ያሉትን ሕመምተኞች ፈውሱ፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች›› ብላችሁም ንገሩአቸው፡፡