\v 43 በዚያም ለአሥራ ሁለት ዓመታት ደም ሲፈሳት የነበረች፣ ገንዘቧን ሁሉ ለሐኪሞች ብትከፍልም አንዳቸውም ያልፈወሷት ሴት ነበረች። \v 44 እርሷም ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ ከእርሷ ይፈስ የነበረው ደም ወዲያው ቆመ።