am_luk_text_ulb/08/40.txt

1 line
614 B
Plaintext

\v 40 ሁሉም ይጠብቁት ነበርና ኢየሱስ ሲመለስ ሕዝቡ ተቀበሉት። \v 41 እነሆም ከምኩራብ መሪዎች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ እርሱም በኢየሱስ እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ ይመጣ ዘንድ ለመነው። \v 42 ወደ ቤቱ እንዲመጣ የፈለገው አሥራ ሁለት ዓመት የሆናት ብቸኛዋ ሴት ልጅ ለሞት ተቃርባ ስለነበረ ነው። ነገር ግን ወደዚያ እየሄደ በነበረበት ጊዜ ብዙ ሕዝብ ይገፉትና ያጨናንቁት ነበር።